በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካሜሩን በቦኮ ሃራም ጥቃት 12 ሰዎች ሞቱ


በካሜሩን ቦኮ ሃራም ባደረሰው ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን የሃገሪቱ ወታደራዊ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ዓሣ በብዛት በሚሰገርባት እና በቻድ እና ናይጄሪያ ወሰን አካባቢ በምትገኘው ‘ዳራክ’ ደሴት ላይ ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በደረሰው ጥቃት የሞቱትን ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ እየቀጠለ ያለው የቦኮ ሃራም ጥቃት አስቸጋሪ ቢያደርገውም፣ 12 አስከሬኖችን ማግኘቱን የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል።

አንዳንድ ነዋሪዎች ጸጥታው ወደ ተሻለ ሥፍራ መሸሻቸውም ታውቋል።

ከፍተኛ ትጥቅ ያነገቡ ነውጠኞች በቻድ ሀይቅ በኩል አድርገው በጀልባ ሰኞ ዕለት እንደደረሱ እና የጥቃቱ ሰለባዎች በሙሉ ዓሣ አስጋሪዎች መሆናቸውን ሠራዊቱ ጨምሮ አስታውቋል።

የናይጄሪያ መንግሥት እና ቦኮ ሃራም ከ14 ዓመታት በፊት የጀመሩት ጦርነት ወደ ቻድ እና ካሜሩን ተዛምቶ 36 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ 3 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያስታውቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG