በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቅዱስ ሲኖዶስ በአክሱም የተፈጸመውን የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት አወገዘ


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ማትያስ እና የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ፣ በጽሑፍ ያነበቡት ዋና ጸሐፊው ብፁዕ አባ ጴጥሮስ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ማትያስ እና የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ፣ በጽሑፍ ያነበቡት ዋና ጸሐፊው ብፁዕ አባ ጴጥሮስ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ዛሬ በአካሔደው አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ፣ ሐምሌ 16 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በትግራይ ክልል በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን፣ በአራት ሊቃነ ጳጳሳት የተፈጸመውን የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት አወገዘ፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በአክሱም የተፈጸመውን የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት አወገዘ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:04 0:00

“የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ሰላም ከፍተኛ ቤተ ክህነት” በሚል ያቋቋሙት ክልላዊ መዋቅም፣ በታሪክ የማይታወቅ እና ትውፊታዊ መሠረት የሌለው ሕገ ወጥ እንደኾነ ገልጾ፣ ለዚኽ እንቅስቃሴ መጀመር ዋና ተጠያቂዎች ናቸው ያላቸውን ሁለት ግለሰቦችንም፣ ከአራቱ ሿሚ ሊቃነ ጳጳሳት እና ከዘጠኙ ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ጋራ አብሮ አውግዟል፡፡ በዛሬው፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ፣ ከትግራይ ክልል አባቶች፣ መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ኾኖም፣ ባለፈው ሳምንት በአክሱም የተፈጸመውን የኤጲስ ቆጶጳት ሹመት አስመልክቶ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራርያ የሰጡት በክልሉ የተቋቋመው መንበረ ሰላማ ከፍተኛ ቤተ ክህነት ጸሓፊ መጋቤ ብርሃናት ተስፋይ ሃደራ፣ “በቤተ ክርስቲያኒቷ ሕግ መሠረት በችግር ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት ጳጳሳት ሌሎች ኤጲስ ቆጶሳትን ይሾማሉ፤ ይላል፡፡

ትግራይ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ችግር ውስጥ ስለምትገኝ፣ ሕዝቡ ተጨማሪ አባት ስለሚያስፈልገው በቀኖናው መሠረት ሾመናል፤" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝርን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG