በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትረምፕ ላይ የተከፈተው የምርጫ-ጣልቃ ገብነት ክስ


የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ

እአአ የ2020ቱ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት “ተሰርቋል” የሚለውን መሠረተ ቢስ ውንጀላ ለዓመታት ሲገፉ የቆዩት የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የተሸነፉበትን የምርጫ ውጤት ለመቀልበስ በማሴር ተወነጀሉ።

“የሙጥኝ ብለው ስልጣን ላለመልቀቅ ያቀዱት እና የምርጫውን ውጤት ለመስረቅ የሞከሩት እርሳቸው ናቸው” ያለው የክሱ መዝገብ ትላንት ማክሰኞ ነው ይፋ የተደረገው። ክሱ አክሎም ትረምፕ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ያሸነፉበትን የምርጫ ውጤት ለመቀልበስ ከአጋሮቻቸው ጋር ሆነው አሲረዋል ይላል።

በመጪው 2024 በሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲያቸው ዕጩ ሆኖ ለመቅረብ በመራጭ ድጋፍ ትንበያዎች ተፎካካሪዎቻቸውን በከፍተኛ ብልጫ እየመሩ ያሉት ዶናልድ ትረምፕ በወንጀል ሲከሰሱ በአንድ ዓመት ብቻ ያሁኑ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG