በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴቶችን የቤት ውስጥ የሥራ ጫና የሚያቃልል “ተግባር ተኰር የባሎች ሥልጠና” በይርጋለም እየሰጠ ነው

የሴቶችን የቤት ውስጥ የሥራ ጫና የሚያቃልል “ተግባር ተኰር የባሎች ሥልጠና” በይርጋለም እየሰጠ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:52 0:00

የሴቶችን የቤት ውስጥ የሥራ ጫና የሚያቃልል “ተግባር ተኰር የባሎች ሥልጠና” በይርጋለም እየሰጠ ነው

ባሎቻቸው፣ ከአራስ ሕፃን ክብካቤ እና አያያዝ እስከ ምግብ ማብሰል የሚያካትት የባሎች ሥልጠና የወሰዱላቸው ሚስቶች፣ በሥራቸው እና በኑሯቸው ለውጥ ማየት እንደጀመሩ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

በሥልጠናው እየተሳተፉ የሚገኙ አባወራዎች እና ዐዲስ ተጋቢዎች፣ የቤት ውስጥ ሥራን አድካሚነት እንድንረዳ፣ የሕይወት አጋሮቻችንም እንድናግዝ አስችሎናል፤ ሲሉ ተናግረዋል።

የግል ሥራ የጀመሩ ወጣት ሴቶችን ውጤታማ ለማድረግ፣ “ዓለም አቀፍ የሕፃናት አድን ድርጅት”፣ከ500 በላይ ባሎችን፣ አባቶቻቸውንና ወንድሞቻቸውን ሥልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ፣ በሕፃናት አድን ድርጅት የአመራር ክህሎት እና የኢኮኖሚ ዐቅም ማጎልበት ፕሮግራም ሓላፊ ስናፍቅሽ ለማ አስታውቀዋል።

ዝርዝርን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG