በዩናይትድ ስቴትስ ለሚያደርገው ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች ትላንት የተጓዘው ብሔራዊው ቡድን ተነገ ወዲያ ረቡዕ ሐምሌ 26 ከጋያና ብሔራዊ ቡድን ፣ ሐምሌ 29 ደግሞ ከአትላንታ ሮቨርስ ክለብ ጋር ጨዋታውን እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡
የሴቶች የዓለም ዋንጫ ጣምራ አስተናጋጇ ኒውዚላንድ ከውድድሩ ተሰናብታለች፡፡ ሞሮካዊቷ ቤንዚና በፊፋ የዓለም ዋንጫ ሂጃብ በመልበስ የመጀመሪያዋ ተጫዋች ሆናለች፡፡
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ጁቬንቱስን ከቀጣዩ የአውሮፓ ውድድር ሲያግድ በቼልሲ ላይም ቅጣት ጥሏል፡፡ የ17 ዓመቱ አሜሪካዊ ብስክሌተኛ ማግነስ ኋይት በልምምድ ላይ እያለ በደረሰበት አደጋ ህይወቱ አልፏል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ሳምንታዊ የስፖርት ፕሮግራም ያድምጡ፡፡
መድረክ / ፎረም