በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩሲያው ጉባኤ የአፍሪካ መሪዎች በእህል አቅርቦት ጉዳይ ላይ መፍትሄ ሳያገኙ ተበተኑ


ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፤ በሴንት ፒተርስበርግ ፣ ሩሲያ
ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፤ በሴንት ፒተርስበርግ ፣ ሩሲያ

ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለሁለት ቀናት ጉባኤ ተቀምጠው የነበሩት የአፍሪካ መሪዎች፣ ከዩክሬን ለዓለም ገበያ እህል መቅረብ እንዲቀጥል ያቀረቡትን ጥያቄ በተመለከተም ሆነ፣ በዛች ሀገር በመካሄድ ላይ ያለው ጦርነት በሚቆምበት ሁኔታ ላይ አንዳች መፍትሄ ላይ ሳይደርሱ ተበትነዋል።

ፑቲን ባለፈው ቅዳሜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ከዩክሬን እህል ወደ ዓለም ገበያ የሚቀርብበትን ስምምነት በዚህ ወር ማቋረጣቸው፣ የእህል ዋጋ እንዲጨምር አድርጎ የሩሲያ ኩባንያዎችን ተጠቃሚ አድርጓል ብለዋል። ሞስኮ የተወሰነውን ትርፍ ከድሃ ሀገራት ጋር እንደምትጋራ ፑቲን ጨምረው ገልጸዋል።

ፑቲን በተጨማሪም ሩሲያ በአፍሪካ መሪዎች የቀረበውን የሰላም ሃሳብ ታጤነዋለች ብለዋል።

ከ25 ሺሕ እስከ 50 ሺሕ ቶን እህል ለስድስት አፍሪካ ሀገራት በነጻ እንደሚሰጥ ፑቲን ቀደም ብለው አስታውቀው ነበር። እነዚህም፤ ቡርኪና ፋሶ፣ ዚምባብዌ፣ ማሊ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ናቸው።

ፑቲን ቃል የገቡት እህል መጠን የተመድ የዓለም የምግብ ፕሮግራም እህል ከዩክሬን በሚወጣበት ስምም ነት መሠረት ገዝቶ ረሃብ ለተጋረጠባቸው ሀገራት ካሰራጨው 725 ሺሕ ቶን እህል ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው ተብሏል።

54 ከሚሆኑት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ውስጥ በጉባኤው የተሳተፉት 17 ብቻ ሲሆኑ፣ ሩሲያ በዩኩሬን ላይ የፈጸመችው ወረራ አሳሳቢነትን ያመለከታል ተብሏል። እ.አ.አ በ2019 በተደረገው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ 43 የአፍሪካ መሪዎች ተገኝተው ነበር። የተሳታፊዎች ቁጥር መቀነስ “በምዕራባውያን ግፊት የመጣ ነው” ስትል ሞስኮ ትከሳለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG