በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዳርፉር ሚሊሽያዎች ግድያ እና አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ የበረታ ግፍ እየፈጸሙ ነው


ጦርነቱን ሸሽተው ቻድ ከሚገኝ መጠለያ ጣቢያ የደረሱ ሱዳናዊያን
ጦርነቱን ሸሽተው ቻድ ከሚገኝ መጠለያ ጣቢያ የደረሱ ሱዳናዊያን
አምና አል-ኑር ሁለት ጊዜ ለጥቂት ከሞት አምልጣለች። የመጀመሪያው በሱዳኗ የዳርፉር ግዛት የቤተሰቦቿን ቤት ሚሊሽያዎች ባጋዩበት ወቅት ሲሆን፤ ከሁለት ወራት በኋላ ደግሞ እርሷንና እና ሌሎች ጦርነቱን በመሸሽ ከቻድ ጋር የሚያዋስነው ድንበር ለመድረስ ሲሞክሩ ሚሊሻዎች ይዘዋቸዋል።
“እንደ በግ ጨፈጨፉን”
“እንደ በግ ጨፈጨፉን” ስትል ባለፈው ሚያዝያ ወር መጨረሻ በትውልድ ከተማዋ ጀኒና ስለደረሰው ጥቃት የተናገረችው የ32 ዓመቷ መምሕርት "ሁላችንንም ከቀያችን ለመንቀል ያደረጉት ነው።" ብላለች፣
አል ኑር እና ሶስት ልጆቿ አሁ ን ያሉት ቻድ ውስጥ ወደ ስደተኞች ካምፕ የተለወጠ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው። ከእልቂቱ የተረፉት እና ሁኔታውን በቅርብ የሚከታተሉ የመብት ተሟጋቾች “የጭካኔ መዓት” ካሉት ጥቃት የሸሹ፣ የሚበዙቱ ሴቶች እና ህጻናት የሆኑ ከ260 ሺህ በላይ ሱዳናውያን ተጠልለዋል ።
ዳርፉር ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት ጃንጃዊድ የአረብ ሚልሻዎች፡ ራሳቸውን ‘ከመካከለኛው እና ከምስራቅ አፍሪካ ወገን’ አድርገው በሚያዩ ህዝቦች ላይ በፈጸሙት የበረታ ግፍ ሳቢያ የዘር ማጥፋት እና የጦር ወንጀል መለያ ምልክት ተደርጋ ትታይ እንደነበር ይታወሳል።

አሁን ደግሞ በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል የቀጠለውን ውጊያ ተከትሎ በዳርፉር እየደረሰ ያለው መጠነ ሰፊ ግድያ፣ የአስገድዶ መድፈር እና የመንደሮች የጅምላ ውድመት፡ የዚያን አሰቃቂ ግፍ ታሪክ እንዳይደግም የሚለው ስጋት እያየለ መጥቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG