በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ የ400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ልታገኝ ነው


A view shows motorists driving along a street in Addis Ababa
A view shows motorists driving along a street in Addis Ababa

ኢትዮጵያ ለትምህርት እና ለሕፃናት ምገባ የሚውል፣ 400 ሚሊዮን ዶላር፣ በርዳታ እና በብድር መልክ፣ ከዓለም ባንክ ልታገኝ እንደኾነ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ትላንት ይፋ አድርጓል።

ከድጋፍ ገንዘቡ 350 ሚሊዮን ዶላር በርዳታ እና 50 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ በብድር እንደተገኘ፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይፋ ያደረገው መግለጫ አመልክቷል።

ገንዘቡ፣ “የልጃገረዶች እና የአዳጊ ልጆችን የትምህርት ውጤት እና አመጋገብ ለማሻሻል፤ የአገልግሎቶችን አቀራረብ እና ተጠያቂነትን ለማጠናከር፣ በግጭት እና በድርቅ የተጎዱ፣ እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ የሚገኙባቸውን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ጥቅም ላይ ይውላል፤” ሲል መግለጫው አብራርቷል።

ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ያጋጠማት ኢትዮጵያ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ ለሁለት ዓመታት የዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና ድርቅ፣ እንዲሁም የጎርፍ አደጋ እና የአንበጣ ወረርሽኝ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ያደረሷቸው ጉዳቶች ጫና አሁንም ድረስ እንደ ጎላ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG