በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜናዊ ምሥራቅ ናይጄሪያ ጂሃዲስቶች 32 ሰዎችን ገደሉ


በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ቦርኖ ክልል፣ ከአይሲስ ጋራ ግንኙነት አላቸው የተባሉ ጂሃዲስቶች ባደረሷቸው ሁለት የተለያዩ ጥቃቶች፣ 32 ሰዎችን እንደገደሉ ኤኤፍፒ ዘገበ፡፡ ከሟቾቹ 25ቱ እረኞች እንደኾኑ፣ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

ጥቃቶቹ፣ ባለፈው ማክሰኞ የተፈጸሙት፣ የአይሲስ የምዕራብ አፍሪካ ክንፍ ሰፊ ግዛትን በሚቆጣጠርበት የቻድ ሐይቅ አካባቢ እንደኾነ ሪፖርቱ አመልክቷል።

በመጀመሪያው ጥቃት፣ ጂሃዲስቶቹ በሞተር ብስክሌት ላይ ተፈናጠው፣ ከብቶቻቸውን ለግጦሽ ያሠማሩ 25 የፉላኒ እረኞችን እንደገደሉ ታውቋል። አጥቂዎቹ፣ ከሟቾቹ እረኞች ላይ ምንም ሳይወስዱ እንደተመለሱ ታውቋል።

“ለአገሪቱ ሠራዊት መረጃ ታቀብላላችኹ፤” በሚል፣ እረኞቹ ከአካባቢው እንዲርቁ፣ ጂሃዲስቶቹ ጠይቀዋቸው እንደነበርም በዘገባው ተመልክቷል።

ቦኮ ሃራም እና ተቀናቃኙ የአይሲስ የምዕራብ አፍሪካ ክንፍ የኾኑት ጂሃዲስቶች፣ “መረጃ ለሠራዊቱ ታቀብላላችኹ፤” በሚል አርሶ አደሮችንና በሌላ ሥራ የሚተዳደሩ የአካባቢውን ነዋሪዎች ማጥቃታቸውን ቀጥለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG