በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓመቱ ሰባት ወራት 900 የሚደርሱ ፍልሰተኞች ሰጥመው እንደሞቱ ቱኒዚያ አስታወቀች


ፎቶ ፋይል፡- የቱኒዚያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ወደ ኢጣሊያ ሊሻገሩ የሞከሩ የአፍሪካ ፍልሰተኞችን ሲያስቆሙ ስፋክስ፣ ቱኒዝያ
ፎቶ ፋይል፡- የቱኒዚያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ወደ ኢጣሊያ ሊሻገሩ የሞከሩ የአፍሪካ ፍልሰተኞችን ሲያስቆሙ ስፋክስ፣ ቱኒዝያ

በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ያለፉት ሰባት ወራት ውስጥ ብቻ፣ 900 የሚደርሱ ፍልሰተኞች፣ በቱኒዚያ በኩል ባለው የሜዲትሬንያን ባሕር ውስጥ ሰጥመው እንደሞቱ፣ የአገሪቱ መንግሥት አስታውቋል።

የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው፣ እስካለፈው ሳምንት ድረስ፣ 901 አስከሬኖችን ከባሕር ውስጥ ሰብስበዋል፡፡

ለተሻለ ሕይወት ፍለጋ፣ ወደ አውሮፓ ለሚጓዙ ፍልሰተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ ቱኒዚያ አማራጭ መተላለፊያ ናት፡፡ የቱኒዚያ ሁለተኛ ከተማ የኾነችው ስፋክስ፣ ከጣልያኗ የስደተኞች መዳረሻ ላምፔዱሳ ደሴት የምትርቀው 130 ኪ.ሜ. ብቻ ነው።

በአመዛኙ ከሰሃራ በታች ከኾኑ ሀገራት የተነሡ 34 ሺሕ ፍልሰተኞችን፣ በባሕር ላይ ከደረሱ አደጋዎች እንደታደገችም፣ ቱኒዚያ አስታውቃለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG