በኦሮሚያ ክልል በእስር ላይ የሚገኙ የኦነግ አመራሮች እንዲለቀቁ፣ ሂዩማን ራይትስ ዎች ጠየቀ፡፡
ፍርድ ቤት፣ ሰባቱ የፓርቲው አመራሮች በነፃ እንዲሰናበቱ ውሳኔ ቢያስተላለፍም፣ ፖሊስ ከእስር አለመልቀቁን የገለጹት፣ የድርጅቱ የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ዲሬክተር ላቲሺያ ባይደር፣ “በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዐቱ ጥያቄ ውስጥ ስለ መኾኑ ማሳያ ነው፤” ብለዋል።
በሌላ በኩል፣ ፍርድ ቤት ነፃ ብሎ ያሰናበታቸውን እስረኞች፣ ከእስር ለማስለቀቅ ያደረጉት የተለያየ ጥረት እንዳልተሳካላቸው፣ የተከሣሾቹ ጠበቃ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ፣ ከመንግሥት አካላት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም