በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ለኢትዮጵያ ድጋፏን እንደምትቀጥል አስታወቀች


የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሓላፊ ዋንግ ዪ፣ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር
የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሓላፊ ዋንግ ዪ፣ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሓላፊ ዋንግ ዪ፣ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን ጋራ፣ በሳምንቱ መጨረሻ ተገናኝተው እንደተነጋገሩ ታውቋል።

የኮሚኒስት ፓርቲው የፖሊት ቢሮ አባልም የኾኑት ዋንግ ዪ፣ ደቡብ አፍሪካ ላይ በሚደረገው የብሪክስ (BRICS) ስብሰባ ላይ ለመገኘት በሚያቀኑበት ወቅት፣ እግረ መንገዳቸውን ወደ ኢትዮጵያ ጎራ እንዳሉ፣ የቻይናው ማዕከላዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ (CCTV) በዘገባው አመልክቷል።

ኢትዮጵያ፣ ብሪክስን ለመቀላቀል ባለፈው ወር እንደጠየቀች ይታወሳል።

“ቻይና፣ ለራሷ የሚስማማውን የልማት ጎዳና አጥብቃ በመያዝ ያስመዘገበችው ኢኮኖሚዊ እና ማኅበራዊ እድገት፣ ለሌሎች አዳጊ ሀገራት ምሳሌ ኾኗል፤” ሲሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንደተናገሩ ዘገባው ጠቅሷል።

እንደ ዘገባው፣ ኢትዮጵያ ችግር በገጠማት ወቅት ኹሉ፣ ቻይና ጠንካራ ድጋፍ በማድረግ ወዳጅነቷን አሳይታለች፤ ሲሉ፣ አክለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ሁለቱ ሀገራት፣ በበርካታ መስኮች ትብብር እንደሚያደርጉ ያወሱት ዋንግ ዪ፣ አገራቸው፥ ኢትዮጵያ በመልሶ ግንባታ እና ኢኮኖሚዋ እንዲያንሰራራ የምታደርገውን ጥረት፣ አገራቸው እንደምትደግፍ ተናግረዋል።

ሓላፊው ዋንግ ዪ፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን ጋራ ባደረጉት ቆይታም፣ ኢትዮጵያ፥ ሉዓላዊነቷንና የግዛት አንድነቷን ለመጠበቅ ከምታደርገው ጥረት ጎን ቻይና እንደምትቆም አረጋግጠዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG