በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተቃዋሚ ሰልፈኞች የባግዳድ አረንጓዴ ቀጠናን ጥሰው ለመግባት ሞከሩ

የጸጥታ ኃይሎች ወደ አረንጓዴው ዞን የሚያመራውን ጃሙሪያ ድልድልይ የተቆጣጠሩትን ተቃዋሚ ሰልፈኞችን በመግፋት ዴንማርክ ኤምባሲ እንዳይደርሱ አግደዋቸዋል።
የጸጥታ ኃይሎች ወደ አረንጓዴው ዞን የሚያመራውን ጃሙሪያ ድልድልይ የተቆጣጠሩትን ተቃዋሚ ሰልፈኞችን በመግፋት ዴንማርክ ኤምባሲ እንዳይደርሱ አግደዋቸዋል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ጠንካራ ጥበቃ የሚደረግለትን ፣የበርካታ ሀገራት ኤምባሲ መገናኛ ፣ እና የኢራቅ መንግስት መቀመጫ የሆነውን የባግዳድ አረንጓዴ ቀጠና በዛሬው ዕለት ጥሰው ለመግባት ሞክረዋል። ይኸውም አንድ አክራሪ ብሄርተኛ ቡድን ዴንማርክ ኮፐንሀገን ከሚገኘው የኢራቅ ኤምባሲ ፊት ለፊት የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ቅዱስ መጽሃፍ የሆነውን ቁርዐን ማቀጣሉ ከተሰማ በኃላ የተደረገ ነው።

የጸጥታ ኃይሎች ወደ አረንጓዴው ዞን የሚያመራውን ጃሙሪያ ድልድልይ የተቆጣጠሩትን ተቃዋሚ ሰልፈኞችን በመግፋት ዴንማርክ ኤምባሲ እንዳይደርሱ አግደዋቸዋል።

የአሁኑ ተቃውሞ ስውዲን ላይ በታቀደው የእስልምና ሃይማኖት ቅዱስ መጽሃፍን የማቃጠል ዕቅድ የተቆጡ ሰልፈኞች በባግደድ የሚገኘውን የስውዲን ኤምባሲ ጥሰው ከገቡ በኃላ የተከሰተ ነው ።

የዲፕሎማቲክ መናጋሻዎችን የተቆጣጠሩት ተቃዋሚዎች ሰንደቅ ዓላማ በማወለብለብ ፣ ተጸዕኖ ፈጣሪውን የኢራቂ ሺቲ እስልምና ዘርፍ መሪዎች እና የፖለቲካ መሪውን ሙክታዳ አል ሳድርን የሚየሳዩ ምልክቶችን አንግበው ለሰዓታት ቆይተዋል። የኤምባሲው ሰራተኞች ከአንድ ቀን በፊት እንዲለቁ ተደርገዋል ።

ባለፈው ወር በስቶክሆልም በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የቁርኣንን ቅጂ ያቃጠለ ኢራቃዊ ጥገኝነት ጠያቂ ያንኑ ድርጊት በድጋሚ ሃሙስ ዕለት ለመፈጸም የዛተ ቢሆንም መጽሃፉን ሳያቃጥል ቀርቷል። ይሁንና መጽሃፉን ፣ የኢራቅ ሰንደቅ ዓላማ እና የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ካሚንን ፎቶ በእግሩ ረጋግጧል።አርብ ከሰአት በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ኢራቅ እና ሌሎች ሙስሊም በሚበዛባቸው ሀገራት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG