በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በሱዳን አገልግሎቱ ቀጣይነት ላይ አደጋ የጋረጠ ጥቃት እንደገጠመው አስታወቀ


ካርቱም፣ ሱዳን
ካርቱም፣ ሱዳን

በትላንትናው ዕለት፣ የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን(MSF) ሠራተኞች የኾኑ 18 የቡድኑ አባላት፣ የሕክምና ቁሳቁሶችን፣ በደቡባዊ ካርቱም ወደሚገኘው የቱርክ ሆስፒታል ለማድረስ በሚያጓጉዙበት ወቅት፣ በቡድን በተደራጁ ታጣቂዎች፣ ዐመፅ የተቀላቀለበት ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ ሲል፣ ተቋሙ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት፣ ኤም.ኤስ.ኤፍ በሥፍራው በመገኘቱ ላይ ከተደረገ ክርክር በኋላ፣ ሠራተኞቹ አካላዊ ግርፊያ እና ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፤ ብሏል፡፡ በተጨማሪም፣ የመሥሪያ ቤቱን ሹፌር አግተው፣ የድርጅቱን መኪና በመቀማት እንደለቀቁት ሲያስታውቅ፣ ሹፌሩ የግድያ ዛቻ ተፈጽሞበታል፤ ብሏል፡፡

ይህን ተከትሎ፣ ተቋሙ፣ በሆስፒታሉ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች አደጋ ተጋርጦባቸዋል፤ ብሏል፡፡ በአሁን ሰዓት፣ በደቡባዊ ካርቱም ርዳታ እየሰጡ ከሚገኙ ሁለት ሆስፒታሎች አንዱ፣ የቱርክ ሆስፒታል ነው፡፡

አሁን የቡድኑን ሠራተኞች የገጠማቸው ጥቃትም፣ በሆስፒታሉ አቅራቢያ የተፈጸመ ሲኾን፣ ሕፃናትን ጨምሮ በ100ዎች የሚቆጠሩ ሕሙማን ያሉበት ነው፡፡ ሆስፒታሉ በየዕለቱ፣ 15 ሕሙማንን ሲቀበል፣ በትላንትናው ዕለት በደረሰ የአየር ድብደባ፣ 44 የሚደርሱ ቁስለኞችን፣ ተቋሙ በሆስፒታሉ ውስጥ እንደተቀበለ አስታውቋል፡፡

የኤም.ኤስ.ኤፍ የሱዳን አጣዳፊ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ ክርስቶፍ ጋርኒየር፣ “የሰዎችን ሕይወት ለማዳን ሲባል፣ በሥፍራው፣ በነፍስ አድን ሥራ ላይ የተሠማሩ ባልደረቦቻችን ሕይወት አደጋ ላይ መውደቅ የለበትም፤” ብለዋል፡፡ አያይዘውም፣ “ከዚኽ በኋላ፣ ይህን መሰሉ ኹኔታ ከተከሠተ እና ቁሳቁሶችን ማጓጓዝ ካልቻልን፣ በሚያሳዝን መልኩ፣ በቱርክ ሆስፒታል ውስጥ የሚኖረን ተደራሽነት የማይቻል ይኾናል፤” ብለዋል፡፡

በአሁን ሰዓት ኤም.ኤስ.ኤፍ፣ በካርቱም ውስጥ ሆስፒታሎችንና የእንባ ጠባቂ ተቋምን እያገዙ ካሉ በጣት ከሚቆጠሩ የሰብአዊ ድጋፍ ተቋማት መካከል አንዱ ነው፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG