በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮሞ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ ተወካዮች እና አምባሳደር ማይክ ሐመር ተወያዩ


ፎቶ ፋይል፦ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር
ፎቶ ፋይል፦ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር፣ በዩናይትድ ስቴትስ ከትውልደ ኢትዮጵያውያን የኦሮሞ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋራ እንደተወያዩ፣ የኦሮሞ ቅርስ አመራር እና ተሟጋች ማኅበር አስታወቀ።

የኦሮሞ ዳያስፖራ ተወካዮቹ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት፣ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጥሎት የነበረውን የርዳታ ማዕቀብ መልሶ ማንሣቱ እንዳሳዘናቸው፣ ለአምባሳደር ማይክ እንደተናገሩ፣ መግለጫው አመልክቷል።
ምክንያት ያደረጉትም፣ በኢትዮጵያ፣ አሁንም አለ ያሉትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በመጥቀስ እንደኾነ፣ ማኅበሩ ገልጿል።
አምባሳደር ሐመር በበኩላቸው፣ የርዳታ ማዕቀቡን የማንሣት ውሳኔ ላይ የተደረሰው፣ ከሀገር ውስጥም ኾነ ከዓለም አቀፍ አካላት በተገኘው መረጃ መሠረት፣ “በተለይም፣ ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚፈጽመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መቀነስ በማሳየቱ ነው፤” ማለታቸውን መግለጫው አስፍሯል።
በሽግግር ፍትሕ ሒደት ውስጥ፣ “የኦሮሚያ ድርሻ ምን ይኾናል?” የሚለውን ጉዳይ፣ ተወካዮቹ ለአምባሳደር ሐመር እንዳነሡላቸው መግለጫው አመልክቷል።

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር መስተጓጎሉን በተመለከተ፣ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ተወካዮቹ ለአምባሳደር ሐመር እንዳነሡላቸውና በዚኽም የዳያስፖራውን ማኅበረሰብ ለመርዳት ያላቸውን ፍላጎት እንደገለጹላቸው፣ መግለጫው አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG