በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ አንዳንድ ቦታዎች ግጭት ቢስተዋልም ተቃውሞው ግን እየቀነሰ ነው


የኬንያ ፖሊስ በተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጋዝ ሲወረውር
የኬንያ ፖሊስ በተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጋዝ ሲወረውር

በኬንያ፣ በትላንትናው ዕለት በአብዛኛው በተቃዋሚው ፓርቲ በተጠራው ሰልፍ ላይ፣ የአገሪቱ ዜጎች በብዛት ባይሳተፉም፣ በአንዳንድ ቦታዎች ግን፣ ድንጋይ በሚወረውሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች እና በፖሊስ መካከል ግጭት ተፈጥሮ ነበር።

ኪብራ በተሰኘው፣ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙና የተቃዋሚው ራይላ ኦዲንጋ ፓርቲ ደጋፊዎች በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ፣ ፖሊስ አስቃሽ ጢስ እና ጥይት መተኮሱን፣ የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተመልክቷል።

ተቃዋሚው ራይላ ኦዲንጋ፣ በሳምንት ውስጥ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ተቃውሞ እንዲደረግ ጥሪ ቢያደርጉም፣ በረቡዕ ተቃውሞ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን፣ የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ኬንያ ቢሮ አስታውቋል።

ካለፈው መጋቢት ወዲህ፣ 20 ሰዎች ከተቃውሞ ጋራ በተያያዘ እንደሞቱ መንግሥት ሲያስታውቅ፣ ፕሬዚዳንቱ ዊሊያም ሩቶ፣ ትላንት ኀሙስ ሰልፉ እንዲቆም በድጋሚ ጥሪ ሲያደርጉ፣የተቃውሞ ሰልፎች ለኬንያ ችግሮች መፍትሔ አያመጡም፤ብለዋል።

የኑሮ ውድነትንና የታክስ ማሻቀብን በመቃወም፣ ኦዲንጋ፣ ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ፣ ሕዝቡ ለተቃውሞ እንዲወጣ ጥሪ አድርገው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG