በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የበረከት ሕይወት የኾነው የወላይታ ሶዶው የእንስሳት ማቆያ- “ጁኒየር ፓርክ”


የበረከት ሕይወት የኾነው የወላይታ ሶዶው የእንስሳት ማቆያ- “ጁኒየር ፓርክ”
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:45 0:00

የበረከት ሕይወት የኾነው የወላይታ ሶዶው የእንስሳት ማቆያ- “ጁኒየር ፓርክ”

ወጣት በረከት ብርሃኑ፣ በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን፣ የሶዶ ከተማ ነዋሪ ነው። ከስድስት ዓመት በፊት ሥራ ዐጥ እንደነበር ገልጿል።

በረከት፣ ሀብት የሚያፈራበት የወጣትነት ዕድሜው፣ እንደ ዋዛ እየነጎዱበት መኾኑን ሲያስተውልና በልቶ ከማደር በቀር ለውጥ የሌለው የድግግሞሽ ሕይወት ሲሰለቸው፣ ሥራ ሳይመርጥ መሥራት እንዳለበት፣ ራሱን እንዳሳመነ ይናገራል።

በረከት፣ በሥራ ራሱን ለመለወጥ ሲያስብ ብቻውን አልነበረም፡፡ አምስት ጓደኞቹ ከእነርሱም ሦስቱ ወንዶች እና ሁለቱ ሴቶች፣ አብረውት ነበሩ። መክረው፣ አውጥተው አውርደው፣ ብዙም እንዳልተለመደ የሚነገረውን፣ የግል የዱር እንስሳት ማቆያ ለመክፈት ወጠኑ።

አጅሪት ጦጢት፣ አያ ጅቦ፣ እነዘንዶ፣ አጅሬው ዓዞ እና ሌሎችንም በውስጡ የያዘ፣ “ጁኒየር ፓርክ” ሲሉ የሰየሙትን የእንስሳት ማቆያ ከፈቱ።

ሰሞኑን ወላይታ፥ ሶዶ ተጉዞ የነበረው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዲዮስ ያሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG