በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ ክሥ የሚሰማበት ቀጠሮ ተሰጠ


የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

በዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ላይ፣ የምስጢራዊ ሰነዶች አያያዝን በተመለከተ፣ የቀረበባቸውን ክሥ ለመስማት፣ ፍርድ ቤት ቀጠሮ ሰጠ።

የክሡ ሒደት፣ ከዘጠኝ ወራት በኋላ፣ እ.አ.አ ግንቦት 20 ቀን 2024፣ ፍሎሪዳ በሚገኘው የፌዴራል ፍርድ ቤት እንዲታይ፣ ዳኛ አይሊን ካነን ቀነ ቀጠሮ ሰጥተዋል። ቀጠሮው፣ በመጪው ዓመት ኅዳር ወር ከሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ስድስት ወር ቀደም ብሎ መኾኑ ነው።

በአሁኑ ወቅት ትረምፕ፣ ሪፐብሊካን ፓርቲውን ለመወከል ከቀረቡት ተወዳዳሪዎች መሀከል፣ ከፊት መሥመር ላይ ይገኛሉ።

ክሡን ያቀረቡት፣ የመንግሥት ዐቃብያነ ሕግ፣ ቀጠሮው ለኅዳር ወር እንዲኾን፣ ባለፈው ማክሰኞ ጠይቀው የነበረ ሲኾን፣ የትረምፕ ጠበቆች በበኩላቸው፣ በአሁኑ ወቅት ቀጠሮ መስጠት አስፈላጊ አይደለም፤ ሲሉ ተከራክረዋል።

ክሥ መስማቱ፣ ለመጪው ነሐሴ ተቀጥሮ የነበረ ቢኾንም፣ ሁለቱም ወገኖች፥ “ለዝግጅት በቂ ጊዜ ያስፈልገናል፤” በማለታቸው ሳይኾን ቀርቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG