ቀደም ሲል፣ በምሥራቅ ቦረና ዞን ጎሮ ዶላ የነበረው የዐዲሱ የምሥራቅ ቦረና ዞን አደረጃጀት ተቃውሞ፣ ወደ ሌሎች የጉጂ ዞን ወረዳዎች እንደተስፋፋ፣ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት፣ ተቃውሞው፣ በተለይ የጎሮ ዶላ ወረዳ አዋሳኝ በኾኑ አዶላ፣ ዋደራ እና ሌሎች ወረዳዎች እንደተስፋፋ፣ መንገድ እና የንግድ ቤቶችም፣ ላለፉት ቀናት ዝግ ነበሩ። የወረዳውን አስተዳደር ጨምሮ፣ ከ20 በላይ የመንግሥት ሠራተኞች፣ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ፣ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
ዐዲሱ የወረዳው አስተዳዳሪ፣ ሓላፊዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፥ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ነው፤ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም