የልዩ ኃይሉን መልሶ የማደራጀት ፕሮግራም አፈጻጸምን ተከትሎ የተፈጠሩ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ማሳደራቸውን የገለጹት፣ የዐማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶር. ይልቃል ከፋለ፣ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ አስታወቁ፡፡
በክልሉ፣ የፌዴራል መንግሥቱ መከላከያ ኃይል እየወሰደ ካለው ርምጃ ጋራ በተያያዘ፣ የጸጥታ ችግሩ አሳሳቢ እየኾነ በመጣበት በዚኽ ሰዓት፣ መደበኛ ስብሰባውን እያካሔደ ለሚገኘው ለክልሉ ምክር ቤት ሪፖርት ያቀረቡት ርእሰ መስተዳድሩ፣ ችግሮችን በሰከነ መንገድ በውይይት መፍታት ይገባል፤ ብለዋል፡፡
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ኤፍሬም አሐዱ፣ የክልሉ መንግሥት፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ እየኾነ በመጣውን የጸጥታ ችግር ጉዳይ፣ ኹሉን አቀፍ ንግግር ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም