በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግጭት እና ግድያ በተባባሰበት የጋምቤላ ክልል ሁሉም ከተሞች የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ


ግጭት እና ግድያ በተባባሰበት የጋምቤላ ክልል ሁሉም ከተሞች የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:44 0:00

ግጭት እና ግድያ በተባባሰበት የጋምቤላ ክልል ሁሉም ከተሞች የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ

በጋምቤላ ክልል በኢታንግ ልዩ ወረዳ በተቀሰቀሰ ግጭት፣ በርካታ ሰዎች እንደተገደሉ እና ሌሎች ብዙዎችም እንደተፈናቀሉ፣ የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

በኢታንግ ወረዳ፣ ከሁለት ወራት በፊት የተቀሰቀሰው ግጭት፣ የብሔር መልክ ይዞ ወደ ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች በመዛመቱ፣ ሰዎች እየተገደሉ እና ለመፈናቀል እየተዳረጉ በመኾኑ፣ በሁሉም የክልሉ ከተሞች የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን፣ የጋምቤላ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ፣ ሰሞኑን አንድ መምሕር እና አንድ ተማሪ፣ በከተማ ውስጥ ባልታወቁ ሰዎች እንደተገደሉበት አስታውቋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አንድ የከተማዋ ነዋሪ፣ ከትላንት ጀምሮ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት መዘጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG