በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዐማርኛ ቋንቋን በድምፅ መተርጎም የሚያስችል ሥራ እየተሠራ ነው


የዐማርኛ ቋንቋን በድምፅ መተርጎም የሚያስችል ሥራ እየተሠራ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:54 0:00

የዐማርኛ ቋንቋን በድምፅ መተርጎም የሚያስችል ሥራ እየተሠራ ነው

በጉግል ትርጉም መተግበሪያ(Google Translation) ላይ፣ እከከ ዛሬ በጽሑፍ ብቻ የሚገኘውን የዐማርኛ ቋንቋ፣ በድምፅም መተርጎም የሚያስችል የመተርጎሚያ ቴክኖሎጂ በመጠናቀቅ ላይ እንደኾነ ተነገረ፡፡
በኢትዮጵያ የጉግል ክላውድሶስርስ ቡድን አስተባባሪ እንደኾነ የገለጸው የቴክኖሎጂ ባለሞያ አብዲሳ ባንጫ፣ ለድምፅ ትርጉሙ አስፈላጊ የኾነው ግብአት፣ ከሦስት ወራት በፊት ተጠናቆ፣ ወደ ጉግል ቋት እንደገባ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግሯል፡፡ የጉግልን ይኹንታ እንዳገኘም፣ አገልግሎት ላይ እንደሚውል አስታውቋል፡፡
ለትርጉም አገልግሎቱ፣ ቀደም ሲል ሥራ ላይ ለዋሉ አራት ተጨማሪ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችም፣ የጉግል ትርጉም መተግበሪያ አገልግሎት በመበልጸግ ላይ እንዳለ፣ አስተባባሪው አብዲሳ ባጫ ተናግሯል፡፡
ይኹን እንጂ፣ እስከ ዛሬ፣ በበጎ ፈቃደኞች የሚሠሩት የትርጉም አገልግሎቶች፣ በሞያው እና በቅንጅት ስለማይሠሩ፣ የማኅበረሰቡንና የግል ባለሀብቶችን ድጋፍ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ እንደኾነ፣ የቴክኖሎጂ ባለሞያው አብዲሳ አመልክቷል፡፡
ቀሪውን ከተያይዘው የድምፅ ፋይል ይመልከቱ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG