በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑቲን በደቡብ አፍሪካ የብሪክስ ስብሰባ እንደማይሳተፉ ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ
ፎቶ ፋይል፦ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በመጭው ነሀሴ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሚካሄደውና በምህጻር “ብሪክስ” እየተባለ በሚጠራው የታዳጊ ኢኮኖሚዎች ቡድን ስብሰባ ላይ እንደማይገኙ ደቡብ አፍሪካ አስታወቀች፡፡

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል አቀባይ ቪንሴንት ማግዌኒያ በሰጡት መግለጫ “በጋራ በተደረሰበት ስምምነት መሰረት ፕሬዚደንት ፑቲን ብሪክስ ጉባዔ ላይ አይገኙም፡፡ በምትካቸው የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሰርጌይ ላቭሮቭ ሩሲያን ወክለው ይገኛሉ” ብለዋል፡፡

በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) በተከሰሱበት የጦር ወንጀል እስር ወንጀል የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ፑቲንን በመሪዎቹን ጉባኤ ለማስተናገድ የፍርድ ቤቱ አባል የሆነችው ደቡብ አፍሪካ አጣብቂኝ ውስጥ ገብታ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ራማፎሳ “ ፑቲን ሀገራችን ቢመጡ እና ብናስራቸው ጦርነት ከማወጅ ይቆጠራል” የሚል ዕምነት ያላቸው መሆኑ ትናንት ተዘግቦ ነበር ፡፡

የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት (አይ ሲ ሲ) ፈራሚ የሆነችው ደቡብ አፍሪካ ግዴታዋን እንድታከብር ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና የመብት ድርጅቶች ወጥረው ቢይዟትም የእስር ማዘዣውን ፈጻሚ ከማድረግ ማምለጫ መንገድ ስትፈልግ ቆይታለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG