ከሳምንታት በፊት፣ ሥፍራውን እንዲለቅ፣ ከዐዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ማሳሰቢያ ተሰጥቶት የነበረው ፈንድቃ የባህል ማዕከል፣ በቦታው ላይ ሊገነባ ያሰበውን ዕቅድ ይዞ እንዲመጣ ተፈቅዶለታል።
ማዕከሉ ብዙ አድናቂዎችን ባፈራበት ቦታ ላይ ዕድሜ ቀጥሎ ይዞታውን እንዲያሻሽል ሲፈቀድለት፣ ደንበኞቹንና ደጋፊዎቹን በእጅጉ አስደስቷል።
የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘጋቢዎች፣ በፈንድቃ የባህል ማዕከል በመገኘት ያጠናቀሩትን ዘገባ፣ ኤደን ገረመው እንደሚከተለው አሰናድታዋለች።
መድረክ / ፎረም