በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዋጋ ንረት እየፈተነው ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ


የዋጋ ንረት እየፈተነው ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:37 0:00

የዋጋ ንረት እየፈተነው ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ

በኢትዮጵያ ለተፈጠረው የዋጋ ግሽበት መባባስ እና የብር የመግዛት ዐቅም መቀነስ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት የሚያካሒደው የብር ኅትመት አስተዋፅኦ ማድረጉን፣ በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ሰውአለ አባተ ገለጹ፡፡

የምጣኔ ሀብት ባለሞያው ፕሮፌሰር ፍሥሓ ጽዮን መንግሥቱ በበኩላቸው፣ የዋጋ ግሽበት፣ ከተጠቀሰው ባሻገር ሌሎች ሀገራዊ ምክንያቶች ቢኖሩትም፣ ብሔራዊ የገንዘብ ቁጥጥር መላላትም የራሱን አስተዋፅኦ አድርጓል፤ ይላሉ፡፡

መንግሥት አሁን የሚታየውን የዋጋ ግሽበት ለማስተካከል፣ ብሔራዊ ባንክ ለገንዘብ ሚኒስቴር የሚሰጠው ብድር በመሠረታዊነት እንዲቀንስ እና ባንኮች ለግሉ ዘርፍ በሚሰጡት ብድር ላይ ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር ለማድረግ ማቀዱን፣ ከብሔራዊ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG