በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካውያን ዲሞክራሲ በትክክል እየሰራ አይደለም አሉ


ፋይል - ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ባንዲራ ዝቅ ብሎ ሲውለበለብ
ፋይል - ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ባንዲራ ዝቅ ብሎ ሲውለበለብ

ቺካጎ ዩንቨርስቲ የሚገኘው ኖርክ የተሰኘ የህዝብ ግንኙነት ምርምር ማዕከል ከአሶስዬትድ ፕሬስ ጋር በመሆን ባለፈው ወር ያካሄዱት አንድ ጥናት አሜሪካውያን ዲሞክራሲ አሁን እየሰራ ባለበት ሁኔታ ደስተኛ አለመሆናቸውን አመለከተ።

በጥናቱ መሰረት፣ ግማሽ የሚሆነው የአሜሪካ ህዝብ ወይም 49 ከመቶው፣ ዲሞክራሲ በትክክል ስራ ላይ እየዋለ አይደለም ያለ ሲሆን፣ ዲሞክራሲ በጣም ወይም እጅግ በጣም ጥሩ ሆኖ እየሰራ ነው ያሉት 10 ከመቶ ብቻ ናቸው። 40 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ እንደነገሩ እየሰራ ነው ብለዋል።

ጥናቱ በተያያዥነት በተመለከተው፣ ሁለቱ ዋና የአሜሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የዲሞክራሲ መርሆዎችን ምን ያክል ያከብራሉ ለሚለው ነጥብ፣ ሁለቱም እጅግ ዝቅተኛ ደረጃዎች አግኝተዋል። በዚህ መሰረት፣ 47 ከመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን ዲሞክራት ፓርቲ የዲሞክራሲ መርሆዎችን ከመከተል አንፃር መጥፎ ስራ እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን 56 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ ሪፐብሊካኖች የተሻለ ስራ መስራት ይችላሉ ብለዋል።

አሶስዬትድ ፕሬስ በበኩሉ፣ የጥናቱ ውጤት፣ በተለያዩ ጫፎች የሚገኙ አመለካከቶች በተስፋፋበት ሀገር፣ ከወረርሽኝ፣ የዋጋ ግሽበት እና የኢኮኖሚ ውድቀት ሊከሰት ይችላል ከሚል ፍርሃት ለመውጣት በሚደረገው ጥረት፣ ሰፊ የፖለቲካ መገለል እንዳለ ያሳያል ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG