በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ባህሪ በተሰኘችው ከተማ ውጊያ አካሄዱ


በሱዳን የሚካሄድው ግጭት ቀጥሎ በካርቱም አቅራቢያ በሚገኘው ባህሪ ጭስ ሲወጣ ይታያል
በሱዳን የሚካሄድው ግጭት ቀጥሎ በካርቱም አቅራቢያ በሚገኘው ባህሪ ጭስ ሲወጣ ይታያል

በሱዳን ሶስት ወር ያስቆጠረውን ግጭት ለማስቆም፣ ሁለቱ ተዋጊ ወገኖች አዲስ የሽምግልና ጥረት በተቀበሉ ማግስት፣ ባህሪ በተሰኘችው ከተማ አንዳንድ ቦታዎች ከፍተኛ ውጊያ ማካሄዳቸውን ነዋሪዎች አስታወቁ።

የሰሜናዊው የባህሪ ከተማ ነዋሪዎች፣ ሁለቱ ተፋላሚዎች ሀልፋያ በተባለው ድልድይ አቅራቢያ ያካሄዱት ውጊያ ጠዋት ከእንቅልፋቸው እንደቀሰቀሳቸው ለሮይተርስ ተናግረዋል። ውጊያው ከሰዓት በኃላም ቀጥሎ፣ የአየር ድብደባ፣ የመድፍ እና የመሳሪያ ተኩስ ድምፅ መስማታቸውንም አመልክተዋል።

በተመሳሳይ ሌሎች የዓይን እማኞች፣ በደቡብ ካርቱም በሚገኘው የጦር ሰፈር አቅራቢያ ውጊያ መካሄዱን ጠቁመዋል።

እ.አ.አ በሚያዚያ 15 የተቀሰቀሰው ጦርነት፣ ሰላማዊ ዜጎችን ከመዲናዋ ካርቱም፣ ባህሪ እና ኦምዱርማን ከተማዎች ያፈናቀለ ሲሆን፣ በዳርፉር ዘርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን አስከትሏል።

በግጭቱ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ቡድኖች በዋና ከተማ የተሰራጩ ሲሆን፣ የሱዳን ጦር ደግሞ ትኩረቱን ያደረገው ብዙም ለውጥ ባላመጣው የአየር እና የመድፍ ጥቃቶች ላይ ነው።

እስካሁን የተካሄዱት ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፍ የሽምግልና ጥረቶች ግጭቱን ማስቆም የተሳናቸው ሲሆን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት፣ ሱዳን ወደ እርስ በርስ ጦርነት ልትገባ ትችላለች ብለዋል።

በቅርቡ በካይሮ የተካሄደውን የሽምግልና ጥረት፣ ከግብፅ ጋር ቅርበት ያለው የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሹ ድጋፍ ሰጪ ቡድን ተቀብለውት ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG