በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዩክሬንና ከሩሲያ እህል ለዓለም ገበያ መጫኑን እንዲቀጥል ጉቴሬዝ ለፑቲን ደብዳቤ ጻፉ


ፎቶ ፋይል፦ ዩክሬን ወደብ እህል እየተጫነ እአአ ሚያዚያ 26/2023
ፎቶ ፋይል፦ ዩክሬን ወደብ እህል እየተጫነ እአአ ሚያዚያ 26/2023

በ“ጥቁር ባሕር ስምምነት” መሠረት፣ እህል ከሩሲያ እና ከዩክሬን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ መጫኑን እንዲቀጥል፣ እንዲሁም ሩሲያ፣ በአተገባበሩ ላይ ያላትን ጥያቄ ለማሟላት ያለመ የመፍትሔ ሐሳብ የያዘ ነው፤ የተባለ ደብዳቤ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ ለሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እንደጻፉ ተገልጿል።

“ምግብ እና ማዳበሪያ፣ ከሩሲያም ኾነ ከዩክሬን በቀጣይነት መውጣቱ፣ ለዓለም የምግብ ዋስትና በሚኖረው አስፈላጊነት ላይ፣ ዋና ጸሐፊው አጽንዖት መስጠታቸውን ይቀጥላሉ፤” ሲሉ፣ የዋና ጸሐፊው ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመት በቱርክ ኢስታንቡል ላይ የተደረሰው ስምምነት፣ ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ ካገደቻቸው ወደቦች፣ እህል ወደ ዓለም ገበያ እንዲቀርብ አስችሎ ነበር። ከስምምነቱ፣ በቂ ጥቅም አለማግኘቷን፣ ሩሲያ በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች፡፡

ከዚኽ በፊት፣ በተወሰኑ ወራት ክፍተት ሲታደስ የቆየው ስምምነት፣ በድጋሚ የመታደሻው ጊዜ፣ ሰባት ቀናት ቀርቶታል፤ ተብሏል።

ሞስኮ ስምምነቱን የማታድስ ከኾነ፣ የዓለም የምግብ ዋጋ መልሶ እንደሚያሻቅብ፣ ባለሞያዎች በመናገር ላይ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG