በአገር ውስጥ፣ በሙስና ወንጀል ክሦች የተጠመዱት የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ፣ ባለፈው ሳምንት፣ በዚምባቡዌ በተካሔደው የአፍሪካ የካርበን ክሬዲት ዓመታዊ ጉባኤ ላይ፣ ቤላሩስን ወክለው ተሳትፈዋል፡፡
ቤላሩስ፣ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ወረራ በመደገፍ፣ አወዛጋቢውን የዋግነር ተዋጊ ቅጥረኛ ቡድን በማስተናገድ ላይ ነች፡፡ ተንታኞች ታዲያ፣ ዙማ፥ የቤላሩስ እና የአፍሪካ ንግድ ማኅበር የቦርድ አባል ለመኾን የበቁት፣ ከዚያች ሀገር ጋራ ባላቸው ቅርብ ግንኙነት እንደኾነ ይናገራሉ፡፡
ኮለምበስ ማቩንጋ ከሐራሬ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም