በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ለዩክሬን ስለምትሰጠው የክላስተር ቦምብ ተገቢነት ተከራከረች


አሜሪካ ለዩክሬን ስለምትሰጠው የክላስተር ቦምብ ተገቢነት ተከራከረች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:08 0:00

አሜሪካ ለዩክሬን ስለምትሰጠው የክላስተር ቦምብ ተገቢነት ተከራከረች

የኔቶ አባል ሀገራት፣ በቪልኒያስ ለሚያደርጉት ስብሰባቸው እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ በርካታ አነስተኛ ቦምቦች የታጨቁባቸውን ትልልቅ የክላስተር ቦምቦች(Cluster Bombs) ለዩክሬን የመስጠት ውሳኔዋን ተገቢነት በድጋሚ አስታውቃለች። ይኹን እንጂ፣ ኪቭ፥ በቅርብ ጊዜ ወደ ኔቶ የመቀላቀል እድሏ የተመናመነ ኾኗል።

ከውስጣቸው ሌሎች አነስተኛ ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን የሚለቁ የክላስተር ቦምቦች፣ ያለምንም ልዩነት ያገኙትን ሁሉ በጅምላ ሊገድሉ ይችላሉ፡፡ ከ100 በላይ የሚኾኑ አገሮች፣ እነዚኽን ቦምቦች አግደዋቸል።

ይኹን እንጂ፣ ዩክሬን፥ በሩሲያ ላይ ለምታካሒደው የመልሶ ማጥቃት፣ የጦር መሣሪያ ክምችቶቿ እየተሟጠጡ ነው፡፡ “ዩናይትድስ ስቴትስ አሁን የተወሰኑትን ለመላክ ተስማምታለች፤” ሲሉ የዋይት ሐውስ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ቃል አቀባይ፣ ጆን ከርቢ፣ “ይህን ሳምንት” ለተሰኘው የኤቢሲ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሳምንታዊ ፕሮግራም ተናግረዋል።

“ልዩነቱን ለማጥበብ፣ መደበኛውን የ155 መድፍ ጥይቶችን ምርት በምናጠናቅቅበት ወቅት፣ በውስጣቸው ክላስተር ቦምቦቹን መያዝ የሚችሉ፣ ተጨማሪ የመድፍ ጥይቶችን እንልካለን፤” ብለዋል ከርቢ።

ቦምቦቹን፣ በዩክሬን ከተሞች አካባቢ በመጠቀም እየተከሠሠ ያለው የሩሲያ መንግሥት ራሱ፣ ርምጃውን አውግዟል። የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች በበኩላቸው፣ ክላስተር ቦምቦቹ፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ስለደቀኑት አደጋ በአጽንዖት ተናግረዋል።

ሲኤንኤን ላይ የቀረቡት ዴሞክራቷ የምክር ቤት አባል ባርባራ ሊ በተመሳሳይ ስጋታቸውን ሲገልጹ፣ “ብዙ ጊዜ ወዲያውኑ አይፈነዱም፡፡ ልጆች ላያቸው ላይ ሊቆሙ፣ ሊረግጧቸውም ይችላሉ፡፡ ያ ፈጽሞ ልንሻገረው የሚገባን መስመር አይደለም፤” ብለዋል።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ፣ በኤቢሲ ቴሊቪዥን ቃለ ምልልሳቸው፣ በዘርፈ ብዙ የጦር መሣሪያዎች ደረጃ የሚያገኙትን ዓለም አቀፍ ድጋፍ አስፈላጊነት በድጋሚ አንሥተዋል።

“ኤፍ-16 ተዋጊ ጀት ወይም የሚያስፈልገን ሌላው የጦር መሣሪያ፣ በፍጥነት የመንቀሳቀስ ዕድል ይሰጠናል፤” ያሉት ዜለነስኪ፣ “ተጨማሪ ሕይወት ለማትረፍና ይዞታችንን ለረጅም ጊዜ አስከብረን እንድንቆይ ይረዳናል፤” ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG