በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤንሻንጉል ጉምዝ ሲቪሎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ


በቤንሻንጉል ጉምዝ ሲቪሎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:29 0:00

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ፣ ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። የከተማው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በዕለቱ ከቀኑ 10:30 ጀምሮ፣ በተለምዶ ቻይና ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ፣ 10 የሚደርሱ ሰላማውያን ሰዎች ሲገደሉ፣ ከዘጠኝ በላይ የሚኾኑቱ ደግሞ ቆስለው በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ፣ ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።

የከተማው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በዕለቱ ከቀኑ 10:30 ጀምሮ፣ በተለምዶ ቻይና ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ፣ 10 የሚደርሱ ሰላማውያን ሰዎች ሲገደሉ፣ ከዘጠኝ በላይ የሚኾኑቱ ደግሞ ቆስለው በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡

ግድያውን የፈጸሙት፣ በጫካ የነበሩና በቅርቡ እርቀ ሰላም ፈጽመው ከገቡ የ“ጉሕዴን ተመላሾች” ውስጥ ትጥቅ ያልፈቱ ኀይሎች እንደኾኑ፣ ያመለከቱት ነዋሪዎቹ፣ ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጀምሮ፣ ወደ አጎራባች ከተማ ፓዌ እየተሰደዱ እንደኾነም አክለው ገልጸዋል፡፡

የጉምዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበር አቶ ግራኝ ጉደታ፣ በሰሞኑ ጥቃት እጃቸው አለበት ስለተባሉ የጉምዝ ታጣቂዎች፣ ከመንግሥት ጋራ ኾነው በማጣራት ላይ እንዳሉና ሲጠናቀቅም መግለጫ እንደሚሰጡ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ ከክልሉ መንግሥት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

XS
SM
MD
LG