በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን በጦርነቱ ምክንያት ጠለፋ እና አስገድዶ መደፈር ጨምሯል ሲሉ የረድዔት ተቋማት አስታወቁ


ሱዳን ሰኔ/ 2015 ዓ.ም
ሱዳን ሰኔ/ 2015 ዓ.ም

በሱዳን ወታደራዊ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት በሴቶች እና ህጻናት ላይ ጠለፋ እና አስገድዶ መደፈር እንዲጨመር ማድረጉን የእርዳታ ተቋማት እና ባለስልጣናት ተናገሩ። ከእነዚህ ወስጥ እድሜያቸው 12 ዓመት የሆናቸው ህጻናት መኖራቸውም ተገልጿል።

የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት የጾታዊ ጥቃት ሰለባዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የዘገበ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ሴቭ ዘ ችልድረን ታዳጊ ልጃገረድ ሴቶች በታጣቂ ተዋጊዎች መደፈራቸው “አስጊ በሆነ” መልክ ጨምሯል ሲል ትላንት ዐርብ አስታውቋል።

ምንም እንኳን ግጭቱን ተከትሎ የተከሰቱ የአስገድዶ መደፈሮች ተጣርተው ቢሰነዱም የሱዳን መንግስት የሴቶች ጥቃት መከላከል ተቋም የተመዘገበው አሃዝ ካለው ሁለት በመቶው ብቻ ነው ብሏል።

ይኸን ተከትሎ አንዳንድ ወላጆች ሴት ልጆቻቸው እንዳይደፈሩ እና ጥቃት እንዳይደርስባቸው በመስጋት እየዳሯቸው መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም ልጃገረዶች ለቀናት ታግተው በቡድን እየተደፈሩ መሆኑንም የሚያሳዩ ሪፖርቶች አሉ።

የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን 4.2 ሚሊየን ሴቶች ለጾታዊ ጥቃት ተጋልጠዋል ያለ ሲሆን ሱዳን በአጠቃላይ 49 ሚሊየን ህዝብ አላት።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ አንዳንድ ልጃገረዶች በደረሰባቸው የአስገዶ መደፈር ምክንያት ወደ ስደተኛ ጣቢያዎች ሲደርሱ ነፍሰጡር ሆነዋል ሲል አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG