በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሕገ ወጥ መንገድ ነዳጅ ጭኗል ያለችውን መርከብ ኢራን መያዟን አስታወቀች


ፋርስ ባሕረ ሠላጤ
ፋርስ ባሕረ ሠላጤ

የኢራን አብዮታዊ ዘብ፤ በሕገ ወጥ መንገድ 900 ቶን ነዳጅ ከ12 ሠራተኞች ጋራ ጭኗል የተባለን የንግድ መርከብ ትላንት ኅሙስ ፋርስ ባሕረ ሠላጤ ላይ መያዙን፣ ‘ፋርስ’ የተሰኘው የኢራን የዜና ወኪል ዘግቧል።

አብዮታዊ ዘቡ የባህር ቅኝት ለማድረግ እና መርከቡን ለመያዝ የፍርድ ቤት ማዘዣ እንዳወጣ ዜና አገልግሎቱ ጨምሮ ገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል ቃል አቀባይ፣ “እስላማዊው አብዮታዊ ዘብ፥ በሕገ ወጥ የኮንትሮባንድ ድርጊት ሳይሠማራ እንደማይቀር የተገመተ፣ አንድ የንግድ መርከብ በኃይል ይዟል፤” ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ስለ ጉዳዩ፣ ወዲያውኑ ተጨማሪ ዝርዝር ማግኘት እንዳልተቻለም ተዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል፣ በዚኽ ሳምንት መጀመሪያ ላይ፣ ኢራን ሁለት የንግድ መርከቦችን ለመያዝ ስትሞክር ያስቆማት መኾኑን የዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል ማዕከላዊ ዕዝ አስታውቋል፡፡

ሚሳዬል ተሸካሚ የአሜሪካ ባህር ኃይል መርከብ በሥፍራው ሲደርስ፣ የኢራኑ መርከብ እንዳፈገፈገ ባህር ኃይሉ ጨምሮ ገልጿል።

መርከቦቹ፣ በዓለም አቀፍ ውኃ ወይም የባሕር ወሰን ላይ እንደነበሩም፣ ማዕከላዊ ዕዙ ገልጿል።

“ከ እ.ኤ.አ 2021 ወዲህ፣ ኢራን፥ ወደ 20 የሚጠጉ ዓለም አቀፍ ሰንደቅ የሚያውለበልቡ የንግድ መርከቦችን አዋክባለች፣ አጥቅታለች ወይም ይዛለች፤” ሲል፣ የዩናይትድ ስቴትስ ባሕር ኃይል በዚኽ ሳምንት አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG