በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ አል-ሻባብ ያደረሰው ከተባለ ጥቃት ተከትሎ 20 ታጣቂዎች ተገደሉ


ፎቶ ፋይል፦ ናይሮቢ፣ ኬንያ

ኬንያን ከሶማሊያ በሚያዋስነው በማንዴራ አካባቢ ትናንት ረቡዕ አልሻባብ ያደረሰው ከተባለ ጥቃት ተከትሎ 20 ታጣቂዎች መገደላቸውን እና 8 ፖሊሶች መጎዳታቸውን የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ ኃይል አስታውቋል።

የልዩ ፖሊስ አባላት በማንዴራ አካባቢ ቅኝት በማድረግ ላይ ሳሉ፣ በደፈጣ ከባድ ተኩስ እንደተከፈተባቸው ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል። ከባድ መሣሪያዎች መውረሱንም አስታውቋል።

ከአል-ቃይዳ ጋር ግንኙነት ባለው በአል-ሸባብ በርካታ ጥቃቶች መፈጸሙ ለረጅም ግዜ ተዘግቶ የቆየውን ሁለቱን አገራት የሚያገናኘውን መንገድ እንደገና የመክፈቱን ጉዳይ እንዳዘገየው የኬንያ መንግስት በትናንትናው ዕለት አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG