በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል የታጋች ቤተሰቦች እና የሰብአዊ መብቶች ተቋማት መንግሥት ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጠየቁ


በኦሮሚያ ክልል የታጋች ቤተሰቦች እና የሰብአዊ መብቶች ተቋማት መንግሥት ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:11 0:00

በኦሮሚያ ክልል የታጋች ቤተሰቦች እና የሰብአዊ መብቶች ተቋማት መንግሥት ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጠየቁ

በኦሮምያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን የሚገኙና ቤተ ሰዎቻቸው በታጣቂዎች የታገቱባቸው ነዋሪዎች፣ ከፍተኛ የማስለቀቂያ ገንዘብ እንደሚጠየቁ ገልጸው ለእንግልት እንደተዳረጉ፣ አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ነዋሪዎቹ፣ ለእገታው ተጠያቂ ያደረጉት፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎችን ነው።

በውጭ አገር የሚኖሩትና የታጣቂዎቹ የበላይ አማካሪ እንደሆኑ የገለጹት አቶ ጅሬኛ ጉደታ፣ ታጣቂዎቻቸው በድርጊቱ ውስጥ እንደሌሉበት ገልጸዋል። “ኾን ተብሎ ሠራዊታችንን ከሕዝቡ ጋራ ለማጋጨት የሚፈጸም ድርጊት ነው፤” በማለት አስተባብለዋል። በጉዳዩ ላይ፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ አላገኘንም።

የዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብቶች ሲቪክ ማኅበራት ጥምረት የኾነው፣ የሰብአዊ መብቶች ድርጀቶች ኅብረት በበኩሉ፣ ዜጎችን ለከፋ እንግልት እየዳረገ ያለውን እገታ ለማስቆም፣ መንግሥት ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG