በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስድስት የደቡብ አፍሪካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ገዥ ፓርቲውን ለመፎካከር ሊቀናጁ ነው


የደቡብ አፍሪካው ተቃዋሚ ዴሞክራሲያዊ ጥምረት ፓርቲ መሪ ጆን ስቴንሁይሰን
የደቡብ አፍሪካው ተቃዋሚ ዴሞክራሲያዊ ጥምረት ፓርቲ መሪ ጆን ስቴንሁይሰን

ስድስት የደቡብ አፍሪካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው ብሄራዊ ምርጫ ጥምረት በመፍጠር ለ30 ዓመታት የቆየውን የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ አገዛዝ እንዲያበቃ ለማድረግ እንደሚመክሩ አስታወቁ፡፡

የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኤኤንሲ)፣ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ መሪ ኔልሰን ማንዴላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁሉን ዘር ባካተተው ምርጫ ንዑሳኑን የነጭ አገዛዝ እ.አ.አ 1994 ካሸነፉበት ጊዜ ጀምሮ የነበሩትን ምርጫዎች በሙሉ ሲያሸነፍ ቆይቷል፡፡

ከዚያ ጊዜ አንስቶ፣ ከእ.አ.አ ከ2009 እስከ 2018 የነበረውን የፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ አስተዳደር ላይ የቀረበውን ለአስርት ዓመታት የሚጠጋውን የወንጀል ክስ ጨምሮ፣ ኤንሲ ለበርካታዎቹ ደቡብ አፍሪካውያን መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማሟላት የተሳነውና ዘወትር በሙስና ቅሌቶች ውስጥ የተዘፈቀ ነው በሚል ይከሰሳል፡፡

ፓርቲው በኢኮኖሚ በበለጸገችው ደቡብ አፍሪካ በየዕለቱ ለሚደርሰው የኤሌክትሪ ኃይል መቆራረጥ ምክንያትም እንደሚከሰስ ተመልክቷል፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የጥምረት ሀሳብ አንድ ፓርቲ ማቋቋም ሳይሆን፣በምርጫው የሚያገኙት ድምር ድምጽ አብላጫውን የጥምር መንግሥት ለመመስረት የሚያስችላቸው እንደሆነ ለመሞከር መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ምንም እንኳ ኤኤንሲ በርካታ ድክመት ቢኖረበትም፣ የታሰበው ስለመሳካቱ ባለሙያዎች ያላቸውን ጥርጥሬ ሰንዝረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG