በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተቃውሞ በቀጠለባት ፈረንሳይ ማክሮን ከከንቲባዎች ጋራ ተወያዩ


የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዒማኑኤል ማክሮን
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዒማኑኤል ማክሮን

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ዒማኑኤል ማክሮን፣ በሰሞኑ ተቃውሞ የተናጡ የ220 ከተሞች ከንቲባዎችን ሰብስበው አነጋግረዋል። ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ፣ አንድ ከሞሮኮ እና ከአልጄሪያ ወላጆች የተወለደ ወጣትን፣ አንድ የፖሊስ አባል ተኩሶ ከገደለ በኋላ፣ በመላዋ ፈረንሳይ በተለይም በምሽት፣ የተቃውሞ ሰልፍ ሲካሔድ ሰንብቷል።

በተቃውሞው፣ 99 ማዘጋጃ ቤቶች ጥቃት ሲፈጸምባቸው፤ ትምህርት ቤቶች፣ ፖሊስ ጣቢያዎች እና ሌሎችም የሕዝብ መገልገያ ተቋማት ዒላማ እንደነበሩ፣ የአገር ውስጥ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ትላንት ሰኞ፣ በርካታ ሰዎች፣ በመላዋ ፈረንሳይ ለተጠቁት ማዘጋጃ ቤቶች፣ አጋርነታቸውን ለመግለጽ ተሰበስበው ነበር።

ተቃውሞዎቹ፣ በአብዛኛው በወጣቶች የተደረጉ ሲሆኑ፣ የሌሎች ሀገራት ተወላጅነት ያላቸው እነዚኽ ወጣቶች፣ በፈረንሳይ መገለል ይደርስብናል፤ የሚል ክሥ ያሰማሉ።

በተቃውሞው ከተያዙት 3ሺሕ354 ሰዎች ውስጥ፣ አማካይ ዕድሜ 17 እንደሆነ፣ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴሩ ጨምሮ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG