በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ሁለት ሚሊሻዎች በታጣቂዎች ተገደሉ


በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ሁለት ሚሊሻዎች በታጣቂዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:33 0:00

በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ሁለት ሚሊሻዎች በታጣቂዎች ተገደሉ

በጋምቤላ ክልል አኙዋ ዞን ዲማ ወረዳ፣ ትላንት፣ ታጣቂዎች ሁለት ሚሊሻዎችን ገድለው አንድ ማቁሰላቸውን፣ የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጽሕፈት ቤቱ ሓላፊ አቶ ኡኬሎ ኡጁሉ፣ ጥቃቱን ያደረሱት ታጣቂዎች ማንነት ለጊዜው እንደማይታወቅ ገልጸዋል፡፡

የክልሉ ጸጥታ እና ሰላም ግንባታ ቢሮ በበኩሉ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሱርማ ወረዳ የሚመጡ ታጣቂዎች፣ ጥቃቱን መፈጸማቸውን ጠቅሶ መሰል ጥቃቶች እንዳይደገሙ፣ ከክልሉ የጸጥታ መዋቅር ጋራ እንደሚወያይ ጨምሮ ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG