በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን: ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የኮሌጅ ተማሪዎችን የአዎንታዊ ድጋፍ ቅበላ ቀሪ የሚያደርግ ውሳኔ እጅግ አሳዝኗቸዋል

ባይደን: ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የኮሌጅ ተማሪዎችን የአዎንታዊ ድጋፍ ቅበላ ቀሪ የሚያደርግ ውሳኔ እጅግ አሳዝኗቸዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:55 0:00

ባይደን: ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የኮሌጅ ተማሪዎችን የአዎንታዊ ድጋፍ ቅበላ ቀሪ የሚያደርግ ውሳኔ እጅግ አሳዝኗቸዋል

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፥ “አዎንታዊ የድጋፍርምጃዎች”(affirmative action) የሚባለውንና በታሪክ፣ በዘር እና በቀለም በመሳሰሉት ማንነቶች፣ ወደ ኋላ የቀሩ ተማሪዎችን፣ የከፍተኛ ትምህርት ዕድልን በእኩልነት ለመስጠት የታለሙ የማጠናከሪያ ድጋፎችን የሚያስተዋውቀውን ፖሊሲ እና አሠራር፣ ቀሪ የሚያደርግ ውሳኔ፣ “እጅግ በጣም አሳዛኝ” ሲሉ ኮንነውታል፡፡

ይሁን እንጂ፣ በትምህርት ውስጥ የሚኖረውን ብዝኀነት፣ ለዘለቄታው የሚያስቀር አይኾንም፤ ብለዋል፡፡ ስድስት ለሦስት በኾነ አብላጫ ድምፅ የተላለፈው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ፣ ዩኒቨርሲቲዎች የሚቀበሏቸውን አመልካች ተማሪዎች ብቃት ለመወሰን፣ ዘርን እንደ መስፈርት መጠቀማቸው ሕገ መንግሥታዊ አይደለም፤ ብሎታል፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የቪኦኤ ዘጋቢ ስቲቭ ሄርማን የላከውንና በአሶሺዬትድ ፕሬስ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG