በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ ተፈናቃዮች በቂ የአፈር ማዳበሪያ እንዳልቀረበላቸው ገለጹ


ኤርትራና ኢትዮጵያ
ኤርትራና ኢትዮጵያ

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ፣ ለአራት ዓመታት ያህል ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የተሰበሰቡ እና ከማኅበረሰቡ ጋራ ተቀላቅለው የቆዩ አርሶ አደሮች፣ ወደ ቀዬአቸው ተመልሰው የግብርና ሥራቸውን ቢጀምሩም፣ በማዳበሪያ እጥረት እንደተቸገሩ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡

በማንዱራ ወረዳ የዳሲኒ ቀበሌ ነዋሪ እንደኾኑ የተናገሩ አንድ አርሶ አደር፣ ከዘመድ አዝማድ በአገኙት ብድር፣ ትራክተር በሄክታር ስድስት ሺሕ ብር ተከራይተው መሬታቸውን ቢያርሱም፣ ማዳበሪያ ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ግብርና ቢሮ በበኩሉ፣ ወደ ክልሉ በቂ ማዳበሪያ እንዳልገባ ገልጿል፡፡

የቢሮ ሓላፊው አቶ ባበክር ሀሊፍ እንደሚሉት፣ ከፌዴራል መንግሥቱ ወደ 300 ሺሕ ኩንታል የሚጠጋ የአፈር ማዳበሪያ ተጠይቆ የቀረበው፣ 111 ሺሕ ኩንታል ብቻ ነው፡፡

የቀረበው ማዳበሪያ በቂ ባለመኾኑ፣ አርሶ አደሩ፥ ሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎችን በቤቱ እንዲያዘጋጅ ሓላፊው አሳስበዋል፡፡

በክልሉ፣ ከ400ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች፣ ቀድሞ ወደነበሩበት አካባቢ እየተመለሱና የእርሻ ሥራቸውን እየጀመሩ እንደኾነ፣ የቢሮ ሓላፊው አክለው ገልጸዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ ተፈናቃዮች በቂ የአፈር ማዳበሪያ እንዳልቀረበላቸው ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:36 0:00

XS
SM
MD
LG