በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጎ አድራጊው ድርጅት 86 ፍልሰተኞችን ከባሕር ላይ ታደገ


አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ ሕፃናት በሚበዙበት አንዲት ትንሽ ጀልባ ላይ የነበሩ 86 ፍልሰተኞችን፣ ከሜዲትሬንያን ባሕር ላይ መታደጉን አስታወቀ፡፡ /ፎቶ፦ ከኤፒ ቪዲዮ ላይ የተነሳ/
አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ ሕፃናት በሚበዙበት አንዲት ትንሽ ጀልባ ላይ የነበሩ 86 ፍልሰተኞችን፣ ከሜዲትሬንያን ባሕር ላይ መታደጉን አስታወቀ፡፡ /ፎቶ፦ ከኤፒ ቪዲዮ ላይ የተነሳ/

አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ ሕፃናት በሚበዙበት አንዲት ትንሽ ጀልባ ላይ የነበሩ 86 ፍልሰተኞችን፣ ከሜዲትሬንያን ባሕር ላይ መታደጉን አስታወቀ።

ከፍልሰተኞቹ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት፣ የመንሳፈፊያ ጃኬት ያላደረጉ ሕፃናት እንደሆኑና ያለአዋቂ እና ጠባቂ እንደተገኙ ታውቋል። አንዳንዶቹ፣ የነዳጅ እና የባሕር ውኃ ቅልቅል በሚፈጠረው ኬሚካል አካላቸው እንደተጎዳ ታውቋል።

ኤስኦኤስ በተባለው መንግሥታዊ ያልኾነ ድርጅት የሚንቀሳቀሰው ኦሽን ቫይኪንግ የተሰኘው የነፍስ አድን መርከብ፣ ከሥፍራው የሦስት ቀናት ጉዞ ርቃ ወዳለችው ባሪ የተባለች የወደብ ከተማ ወስዷቸዋል።

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር እንደሚለው፣ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት፣ 81ሺሕ254 ፍልሰተኞች፣ ከሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ ተነሥተው አውሮፓ ሲገቡ፣ 1ሺሕ208 የሚሆኑቱ ግን፣ ሜዲትሬንያን ባሕርን በማቋረጥ ላይ ሳሉ ጠፍተዋል።

XS
SM
MD
LG