በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፈረንሳይ የወጣቱን በፖሊስ መገደል መነሾ ያደረገው ተቃውሞ ቀጥሏል


አመጽ በፈረንሳይ ሰኔ 22/ 2015
አመጽ በፈረንሳይ ሰኔ 22/ 2015

በፈረንሳይ፣ አንድ የ17 ዓመት ወጣት፣ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ፣ በፖሊስ መገደሉን ተከትሎ፣ በመላ አገሪቱ ተቃውሞው በመደረግ ላይ ነው።

ፖሊስ፥ 150 የሚሆኑ ተቃዋሚዎችን በቁጥጥር ሥር ማድረጉን ሲያስታውቅ፣ ፕሬዚዳንት ዒማኑኤል ማክሮን ከካቢኔያቸው ጋራ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚቀመጡ ተመልክቷል።

ናሄል በሚል የመጀመሪያ ስሙ ብቻ የተለየው የ17 ዓመቱ ወጣት፣ የሰሜን አፍሪካ ትውልድ እንደሆነ ሲነገር፣ ናንቴር በተባለችው እና የሠራተኛው መደብ በሚኖርባት ከተማ እንደተገደለ ለማወቅ ተችሏል። የአሁኑ ዋና የተቃውሞ ማዕከልም፣ ይህቺው ከተማ እንደሆነች ታውቋል።

ተቃውሞው፥ ቱሉስ፣ ዲዦን እና ሊዮን በተባሉ ከተሞች መስፋፋቱም ተነገሯል። የአገሪቱ ፕሬዚደንት ዒማኑኤል ማክሮን፣ ከፍተኛ ሚኒስትሮቻቸውን፣ ለአስቸኳይ የቀውስ አያያዝ ስብሰባ፣ ዛሬ እንደጠሩ ታውቋል።

የወጣቱ መገደል፣ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸውና የተለያዩ ሀገራት ትውልዶች ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው አካባቢዎች፣ የፖሊስን ጭካኔ ያሳያል፤ የሚለውን የነዋሪዎች ክሥ፣ በአደባባይ መነጋገሪያ አድርጎታል፡፡

በግድያው በተጠረጠረው ፖሊስ ላይ ምርመራ በመደረግ ላይ ሲኾን፣ ዐቃቤ ሕግ፥ ሟቹ መኪናውን እንዲያቆም በፖሊስ የተሰጠውን ትዕዛዝ አላከበረም፤ ሲል ርምጃውን አስረድቷል ተብሏል።

XS
SM
MD
LG