በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የልጆች አለኝታ የወላጆች እፎይታ ዴቦራ ፋውንዴሽን ከሕይወት ክህሎት ወደ መደበኛ ትምህርት


የልጆች አለኝታ የወላጆች እፎይታ ዴቦራ ፋውንዴሽን ከሕይወት ክህሎት ወደ መደበኛ ትምህርት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:47 0:00

የልጆች አለኝታ የወላጆች እፎይታ ዴቦራ ፋውንዴሽን ከሕይወት ክህሎት ወደ መደበኛ ትምህርት

በፅንስ አፈጣጠር ወቅት ከሚከሠተው የዘረ መል ተሸካሚ ቁጥር መዛባት (Down syndrome) ጋራ የተወለዱ ሕፃናትንና አዳጊዎችን በመርዳት ላይ የሚገኘውን፣ የዴቦራ ፋውንዴሽን መደበኛ ትምህርት የመስጠት እንቅስቃሴውን ጀምሯል።

ከዘረ መል ተሸካሚ ቁጥር መዛባት ጋራ ተያይዞ በተፈጥሮ ከሚከሠተው ከዚኽ የጤና ችግር (Down syndrome) ጋራ በተወለደች ልጃቸው ዴቦራ ምክንያት፣ ፋውንዴሽኑን ያቋቋሙት አቶ አባዱላ ገመዳ ናቸው፡፡ ፋውንዴሽኑ፥ ችግሩ ላለባቸው ሕፃናት እና አዳጊዎች፣ ትምህርትንና ሥልጠናን ጨምሮ፣ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ፋውንዴሽኑ፣ በቀጣዩ የትምህርት ዘመን፣ ከሙዓለ ሕፃናት ጀምሮ ትምህርት ለመስጠት ተዘጋጅቷል። በተቋሙ ልጆቻቸውን በማስተማር ላይ የሚገኙ ወላጆች፣ የተቋሙ አገልግሎት እና ቀጣይ ዝግጅት፣ የኅሊና ዕረፍት እንደሰጣቸው ተናግረዋል፡፡

ኬኔዲ አባተ፣ የፋውንዴሽኑን መሥራች እና ሌሎችንም አካላት አነጋግሮ ያሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG