በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትራምፕ በ“ጥብቅ ምስጢራዊ” ሰነድ ላይ ሲወያዩ የተቀረፀ ድምፅ ይፋ ሆነ 


የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ
የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ እ.አ.አ በ2021 ሥልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ፣ ከአንድ ጸሐፊ ጋራ ሲነጋገሩ፣ ኢራንን ለማጥቃት ስለተያዘ ዕቅድ የሚያትቱ ምስጢራዊ ሰነዶችን እንደተወያዩ፣ ልዩ ልዩ የዜና ማሠራጫ ተቋማት ይፋ በአደረጉት የድምፅ ቅጂ ተሰምተዋል፡፡

የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ፣ ምስጢራዊ የመንግሥት ሰነዶችን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ይዞ በመቆየት እና የፌዴራል ምርመራ ሒደትን ለማደናቀፍ በማሤር፣ ባለፈው ወር በትራምፕ ላይ በመሠረተው ክሥ፣ ከድምፅ ቅጂው የተወሰነውን ክፍል በማስረጃነት አቅርቧል።

ሲኤንኤን፣ ዋሽንግተን ፖስት እና ኒው ዮርክ ታይምስ የተባሉት የአሜሪካ ብዙኃን መገናኛዎች፣ ትላንት ሰኞ ይፋ ባደረጉት የድምፅ ቅጂ፣ የአሜሪካ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ማርክ ሚሌይ፣ ትራምፕ፥ እ.አ.አበ2020 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን ሲሸነፉ ከኢራን ጋር ግጭት ሊፈጥሩ ይችላሉ፤ ሲሉ ስጋታቸው የገለጹበትን ሪፖርት፣ ትራምፕ ሲጠቅሱ ይሰማሉ።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት፣ “ኦቫል ኦፊስ” ከተሰኘው ጽ/ቤታቸው ወደ ዋይት ኃውስ መኖሪያ ቤት የተወሰዱት ሰነዶች፣ የምስጢራዊነታቸው ደረጃ እንዲነሳ ትዕዛዝ ሰጥተው እንደነበር ገልጸዋል። ይኹን እንጂ፣ ይፋ በተደረገው የድምፅ ቅጂ፣ ትራምፕ፣ ሰነዶቹ በርግጥም ምስጢራዊ እንደነበሩ አምነዋል።

እ.አ.አ በ2024 ለሚካሔደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ ለፓርቲያቸው ግንባር ቀደም ዕጩ ኾነው የሚመሩት ትራምፕ፣ “ምስጢራዊ ሰነዶችን አላግባብ በመያዝ” በሚል፣ ባለፈው ሳምንት የተመሠረተባቸው ክሥ፣ ለመጪዎቹ ወራት፣ በአሜሪካ የፖለቲካ ተዋስኦ የበላይነቱን ይይዛል፤ ተብሎ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG