በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቃዋሚዎች ይዞታ በሆነው በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በተደረገ የአየር ድብደባ ዘጠኝ ሰዎች ሞቱ


ሰሜን ምዕራብ ሶሪያ 2023
ሰሜን ምዕራብ ሶሪያ 2023

ዛሬ ጠዋት በሰሜን ምዕራባዊ ሶሪያ በሚገኘው የተጨናነቀ የአትክልት ገበያ ላይ የአየር ድብደባ ተፈጸመ። በድብደባው ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስታውቀዋል።

ተቀማጭነቱን እንግሊዝ ያደረገ የሶሪያ የሰብዓዊ መብት ታዛቢ እና የጦርነት ዘጋቢ ቡድን የሶሪያው ፕሬዘዳንት በሽር አሳድ ዋና ደጋፊ የሆነችው ሩሲያ፤ የተቃዋሚዎች ጥብቅ ስፍራ የሆነችው እና በቱርክ ድንበር አካባቢ የምትገኘውን ጂስር አል ሹጉር የተሰኘች መንደር ላይ የአየር ጥቃት አድርሰዋል ብሏል።

ጥቃቱ የሩሲያ ዋና ተዋጊ ቡድን በብላድሚር ፑቲን ላይ ባመጸ በማግስቱ ተፈጽሟል። ሰሜን ምዕራብ ሶሪያን የያዙት ባለነጭ ቆብ በመባል የሚታወቁት የሀገሪቱ ተቃዋሚዎች፤ በጥቃቱ እስካሁን ድረስ ከ30 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን እና ይሄ አሃዝም ከፍ እያለ ሊሄድ እንደሚችል አስታውቀዋል።

“ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ ህይወታቸው እያለፈ መሆኑን እየሰማን ነው” ሲሉ የነጭ ቆብ አባል የሆኑት አህመድ ያዚጂ ለአሶሺየትድ ፕሬስ አስታውቀዋል። አያይዘውም “ጥቃቱ ከሰሜን የሀገሪቱ ክፍል የሚመጡ ገበሬዎች የሚሰባሰቡበትን የአትክልት ገበያ ትኩረቱ አድርጓል” ብለዋል።

በጥቃቱ ዙሪያ ሶሪያም ሆነች ሩሲያ እስካሁን ድረስ የሰጡት አስተያየት የለም። ጥቃቱ የተፈጸመበት ሰሜን ምዕራብ ሶሪያ፤ ሃያት ታህሪር አል ሻም በተሰኙት እና በቱርክ የሚደገፉ የመንግስት ተቃዋሚዎች የሚገኙበት ስፍራ ነው።

XS
SM
MD
LG