በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታሊባን መሪ በአፍጋኒስታን የኦፒየም ምርት ቆሟል አሉ


የኦፒየም እርሻ
የኦፒየም እርሻ

የአፍጋኒስታን ዋና መሪ ሀገሪቱ ህገወጥ የመድሃኒት እና የሀሺሽ ምርትን ለማስቆም በምታደርገው ዘመቻ ሄሮይን እና ሞርፊን ለመስራት የሚጠቅሙትን የኦፒየም እንቡጥ ተክሎችን ማውደሟን አስታወቁ።

የሂባቱላህ አክሁንድዛዳ አዋጅ፤ የዩናይትድ ስቴትስ እና የተባበሩት መንግስታት ሪፖርቶች እና የሳተላይት ምስሎች ዓመታዊ የአፍጋኒስታን የኦፒየን ተክል የማሳ ምርት፤ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሰን ካስታወቁ በኋላ ነው።

የምርት መቀነስ የታየው የታሊባኑ መሪ በአውሮፓዊያኑ ሚያዚያ 2022 ኦፒየምን በህገወጥ መንገድ የመትከል፣ የማምረት፣ የመጠቀም፣ የማጓጓዝ፣ የመሸጥ፣ ወደ ውጭ ሃገራት የመላክም ሆነ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትን ካገዱ በኋላ ነው። ክልከላው የታሊባን ጸረ-ናርኮቲክ ቡድን ጦርነት በጎዳቸው የሀገሪቱ ክፍል ያሉትን እና የአለም 85 ከመቶ የሚሆነውን የኦፒየም ምርት የያዙትን ማሳዎች እንዲያወድም አግዟል።

ሀገሪቱ ለኢድ አል አድሃ እየተዘጋጀች ባለችበት ሰዓት ንግግራቸውን ያደረጉት የታሊባን መሪ “ገበሬዎች ህጋዊ የሆኑ ሌሎች አማራጮችን እየፈለጉ ነው” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “እጅግ ብዙ ዜጎች እና የአፍጋን ወጣቶች ለአደጋ ከመጋለጥ ድነዋል” ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት መቀመጫቸውን አፍጋኒስታን ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት ልዑክ የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ባደርጉት ንግግር፤ የታሊባን የኦፒየን ልማትን የማጥፋት ዘመቻ "በስኬት ተጠናቋል" ብለዋል። በተመሳሳይ “የኦፒየም ምርት የሀገሪቱን የገጠር ገበሬዎች የኑሮ ዋልታ በመሆኑ የረድኤት ተቋማት በዚህ ክልከላ የሚጎዱ ገበሬዎች አማራጭ ምርት እንዲጠቀሙ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል” ብለዋል።

በአፍጋኒስታን የዩናይትድ ስቴትስ ተወካይ ቶማስ ዌስት ባለፈው ሳምንት ባደረጉት የትዊተር መልዕክታቸው የኦፒየም ምርት ቅነሳውን አወድሰዋል።

XS
SM
MD
LG