የሴራሊዮን የምርጫ ኮሚሽን በሀገሪቱ እተደረገው ምርጫ ግጭቶች እና፣ መዘግየት ቢታይም ምርጫው አልቆ ቆጠራ በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ ነው ሲል አስታወቀ።
ኮሚሽኑከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የተሰባሰቡት የምርጫ ኮሮጆዎች በፍሪታውን፣ ቦ፣ ከነማ እና ማከኒ ፖርት ሎኮ በተባሉ ቦታዎች ላይ ቆጠራ ይደርገባቸዋል ብሏል። ትላንት ቅዳሜ ሲራሊዮናዊያን፣ የፕሬዘዳንት፣ የፓርላማ እና የአካባቢ ተወካዮች ምርጫ አድርገዋል።
የምርጫ ውጤቶቹ ከ48 ሰዓታት በኋላ ይታወቃሉ። በተመሳሳይ የምዕራብ አፍሪካ የሰላም ግንባታ ትስስር እና ሌላ ታዛቢ ቡድን ምርጫው አንጻራዊ በሆነ ሰላም ተፈጽሞ ቆጠራ እየተደረገ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።