በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለዓመታዊ የሀጅ ጉዞ ወደ 1.5ሚሊዬን የሚጠጉ ሙስሊሞች በሳውዲ አረቢያ ተገኝተዋል።


የሳዑዲ አረቢያ ባለስልጣናት እስካሁን ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ የውጭ ሀገር ምዕመናን ወደ ሀገሪቷ መግባታቸውንና አብዛኞቹ በአየር መጓጓዣ ወደ ሀገሪቱ መድረሳቸውን ተናግረዋል ።
የሳዑዲ አረቢያ ባለስልጣናት እስካሁን ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ የውጭ ሀገር ምዕመናን ወደ ሀገሪቷ መግባታቸውንና አብዛኞቹ በአየር መጓጓዣ ወደ ሀገሪቱ መድረሳቸውን ተናግረዋል ።

ሙስሊም ሃይማኖታዊ ተጓዦች ዓመታዊው ሀጂ በቀጣይ ሳምንት ከመጀመሩ አስቀድመው ወደ ቅድስቲቱ የሜካ ከተማ እየጎረፉ ነው። የዘንድሮ ሀጂ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ለሶስት አመታት ከቆየው ከባድ እገዳ በኋላ ዓመታዊውን ክንውን ወደ ቀደመው ከፍታው ይመልሳል ተብሎ ይጠብቃል።


የሳዑዲ አረቢያ ባለስልጣናት እስካሁን ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ የውጭ ሀገር ምዕመናን ወደ ሀገሪቷ መግባታቸውንና አብዛኞቹ በአየር መጓጓዣ ወደ ሀገሪቱ መድረሳቸውን ተናግረዋል ።ተጨማሪ ተጓዦችም ይጠበቃሉ።ከዚህ በተጨማሪ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሳውዲ አረቢያዊያን እና ሌሎች በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ህዝቦች የሀጅ ጉዞው ስነ-ስርዓት ሰኞ በይፋ ሲጀመር ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሳዑዲ ባለስልጣናት የሀጃጆች ቁጥር ከወረርሽኙ በፊት በነበረበት ቁጥር ይደርሳል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል። በ2019 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ከ2.4 ሚሊዮን በላይ ሙስሊሞች የሀጅ ጉዞ ከውነዋል።

በትናንትናው ዕለት ምዕመናን ሳምንታዊውን የጋራ ጸሎት ለመታደም በሜካ የሚገኘውን ታላቁን መስጂድ ሞልተው ታይተዋል። ብዙዎቹ ምዕመናን በታላቁ ቅዱስ መስጂድ መሀል የሚገኘውን ካባ ዙሪያ ሰባት ጊዜ ዞረዋል ።

ሐሙስ ምሽት ፣ በካባ ዙሪያ ያለው ሰፊ የእብነበረድ እልፍኝ ትክሻ ለትክሻ ሆነው በሚራመዱ አማኞች ተሞልቶ ታይቷል ። ይህ ከሁለት ዓመት በፊት ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ከታዩት ትዕይንቶች የተለየ ነው።

ሀጅ ከአምስቱ የእስልምና መሰረቶች አንዱ ሲሆን ሁሉም ሙስሊሞች የአካል የእና የገንዘብ አቅማቸው ከፈቀደ በሕይወታቸው ቢያንስ አንድ ጊዜ ማከናወን ይጠበቅባቸዋል። በዓለም ላይ ካሉ ታላላቅ ሃይማኖታዊ አብሮነቶች አንዱም ነው።

XS
SM
MD
LG