በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግሉ የጤና ዘርፍ በክፍያ መወደድ ከኅብረተሰብ ተደራሽነት እየራቀ እንደኾነ ኢሰመኮ ገለጸ


የግሉ የጤና ዘርፍ በክፍያ መወደድ ከኅብረተሰብ ተደራሽነት እየራቀ እንደኾነ ኢሰመኮ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:28 0:00

የግሉ የጤና ዘርፍ በክፍያ መወደድ ከኅብረተሰብ ተደራሽነት እየራቀ እንደኾነ ኢሰመኮ ገለጸ

በኢትዮጵያ፣ የግሉ የጤና ዘርፍ አገልግሎት፣ ከኅብረተሰቡ የመክፈል ዐቅም በላይ እየኾነ መምጣቱን፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

በመግለጫው ዙርያ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት፣ በኮሚሽኑ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶር. አብዲ ጅብሪል፣ ተቋማቸው፥ በዘርፉ፣ ከተደራሽነት አኳያ ክትትል ማድረጉን ጠቅሰው፣ የግል የጤና ተቋማት፣ በክፍያ መወደድ ምክንያት፣ ለኅብረተሰቡ በሚፈለገው ደረጃ ተደራሽ እንዳልኾኑ አረጋግጠናል፤ ብለዋል፡፡

የግል የጤና ተቋማትን ያቀፈው፣ የኢትዮጵያ ጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን በበኩሉ፣ አገልግሎቱ የተወደደው፥ በመንግሥት ሊፈቱ የሚገባቸው ችግሮች ስላሉ እንደኾነ አመልክቷል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ደግሞ፣ ለዘርፉ ልዩ ልዩ ድጋፎችን እያደረገ እንደኾነ ገልጾ፣ አሁንም ያሉትን ችግሮች፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋራ በምክክር ለመፍታት፣ ጥናት እየተካሔደ እንደሚገኝ አመልክቷል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG