በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአካል ጉዳተኛው ማርክ “የአካል ማጠንከሪያ ማዕከል” ፈለግ


የአካል ጉዳተኛው ማርክ “የአካል ማጠንከሪያ ማዕከል” ፈለግ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:03 0:00

የአካል ጉዳተኛው ማርክ “የአካል ማጠንከሪያ ማዕከል” ፈለግ

በደቡባዊ የአሜሪካ ግዛቶች፣ “ስፕሊት ሰከንድ ፊትነስ ሴንተር” የተሰኘ የስፖርት ማዕከል፣ ከሜክሲኮ ባሕረ ሠላጤ ጋራ በሚዋሰኑት የዩናይትድ ስቴትስ ክፍላተ ሀገር ተመሥርቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ዋና ትኩረቱን፣ በአካል ጉዳተኞች ላይ ያደረገው የስፖርት ማዕከሉ፣ በዐይነቱ የመጀመሪያ የአካል ማጠንከሪያ ማዕከል ነው።

በሉዊዚያና ክፍለ ሀገር ኒው ኦርሊየንስ ከተማ የሚገኘው ማዕከል መሥራች ማርክ ሬይመንድ ይባላል። ማርክ፣ ይህን የአካል ጉዳተኞችን ጤና እና አጠቃላይ ደኅንነትን የሚያሻሽሉ መርሐ ግብሮች ያሉትን ማዕከል ለማቋቋም ያነሣሣው፣ የራሱ ተሞክሮ እንደኾነ ይናገራል።

ማርክ እ.አ.አ በ2016፣ በውኃ ዋና ላይ ሳለ፣ ጥልቀት በሌለው ውኃ ውስጥ ሲገባ፣ አንገቱ እና የአከርካሪ አጥንቱ በመጎዳቱ፣ እግሮቹም እጆቹም አይታዘዙለትም። ማርክ ከአጋጠመው ከባድ የአካል ጉዳት እንዲያገግም፣ ከፍተኛ የሕክምና ርብርብ እንደተደረገለት ይገልጻል። እርሱ ያገኘውን ክብካቤ ለማግኘት ያልቻሉ፣ ሌሎች ብዙዎች እንዲያገኙ ለማብቃት መነሣሣቱን አስረድቷል።

ፌዶር፣ በሉዊዚያና ኒው ኦርሊየንስ ከተማ የሚገኘውን ማዕከል ጎብኝቶ በአጠናቀረው ዘገባ እንቅስቃሴውን ያስቃኘናል።

XS
SM
MD
LG